
በእግዚአብሔር እርዳታ እና ፀጋ ታላቅ እውነት (Great Truths) አድማሱን በማስፋት በአማርኛ ቋንቋ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርትን በተለያዩ አማራጮች ይዞ መጥቷል። በዚህም ስራው በቤንጃሚን ዲን የተፃፈውን እና ሁለት ከፍል ያለውን “የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ” የተሰኘውን መፅሐፍ ወደ አማርኛ በመተርጎም በፅሁፍ እና በድምፅ አማራጮች አቅርቧል። ይህንኑ መፅሐፍ በቀላሉ ሊደመጥ በሚችል መልኩ በሁለት ሳምንት አንድ ግዜ በሚቀርብ ፖድካስት በተከታታይ ለማድረስ ዝግጅቱን ጨርሷል። ስለዚህም ድጋፍ እና ፀሎታችሁ አይለየን እያልን “ታላቅ እውነት”ን ለሌሎች በማጋራት ተደራሽነታችንን እንድታሰፉ በትህትና እንጠይቃለን።